የአቶ ፉኮ ቡቻላ አጭር   ምስክርነት

 20150612_173615

አቶ ፉኮ ቡቻላ በሲዳማ ዞን በሀገረ ሰላም አካባቢ ቡርሳ በሚባል ስፍራ ተወልዶ ያደጉ ሲሆኑ የተወለዱት የባዕድ አምልኮ ከሚያመልኩ ቤተሰብ እንደነበሩ ይመሰክራሉ፡፡ ገና በተወለዱበት አካባቢ እየኖሩ ሳሉ እግዚአብሄር ሌሊት በህልም እንደጠራቸዉና በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ እንደነገራቸወና ከዚያችም እለት ጀምሮ ጌታን እያገለገሉ መቆየታቸዉን ይመሰክራሉ፡፡ ጌታ በድንቅ አጠራሩ እንደጠራቸዉ በቤቱ እንደተከላቸዉም በምስጋና ይመሰክራሉ፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከማያመልኩና የባዕድ አምልኮን ከሚከተሉ ቤተሰብ የተወለዱ አቶ ፉኮ ቡቻላ ልክ እንደ አብርሃም ከተወለዱበት ስፍራ የወጡት ብርቅ የሆነዉን የእግዚአብሄር ቃል ብቻ አንግበዉ ነበር፡፡  የወንጌል እዉነት ሰንቀዉ ቡርሳ ቦዴ ከሚባል ከተወለዱበት ሥፍራ ለቀዉ ወደ ሀረና ጫካ ሐሊላ ወደሚትባል ሥፍራ ሲያመሩ ተስፋቸዉን የጣሉበት ፣ ያመኑት፣ የተመኩበትና የተደገፉት የአብርሃም አምላክ ብቻ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ አቶ ፉኮ ያልተማሩና ፊደል ያልቆጠሩ ቢሆኑም የተደገፉት ጌታ አያሳፍርምና ምንም ወንጌል ባልደረሰባቸዉ ስፍራ ታላቅ ፍሬን ለማፍራት ቻሉ፡፡ ወደ ሀረና ሲሄዱ ምንም የክርስትና እምነት ተከታይ እንዳልነበረና ወንጌልን ለማዳረስ ብርቱ ተጋድሎ ያደርጉ እንደነበር ይመሰክራሉ፡፡ ስለዚህ በሰፈሩበት አካባቢ የወንጌልን እዉነት ለማብራት በቁርጠኝነት ከመነሳታቸዉም ባሻገር ከባሌ ክፍለ ሀገር በወርቃ ተመድበዉ ከሚያገለግሉና ወደ ወርቃ አካባቢ እየተመላለሱ ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ማለትም ከነ አቶ ቶማስ ሶዳኖ እና አቶ ነጋሽ ደገፉ ጭምር ተጨማሪ ትምህርት ያገኙ እንደነበሩም ይናገራሉ፡፡ በአካባቢ ላሉት ነዋሪዎች ባለመሰልቸት ወንጌልን በመመስከር ፣ ወጣቶችን በማስተማር ፣ ያመኑትን ደቀ መዛሙርት በማድረግ ፣ አዳድስ ነፍሳትን በማስተማር ለብቻቸዉ ሆነዉ ከፍተኛ ተጋድሎ እንዳደረጉ ባደረግንላቸዉ ቃለ መጠይቅ አስቀምጠዋል፡፡ ዛሬ ግን ብዙ አማኞችን ሲያዩና ለረጅም ጊዜ ስጽልዩ የነበሩትን ፍሬ ሲመለከቱ እግዚአብሄርን ያመሰግናሉ፡፡ በሀሊላ ሀዳ አካባቢ ያለዉ የወንጌል ስራ አቶ ፉኮ በጌታ ብርታት ያፈሩ መሆናቸዉን ይናገራሉ፡፡

አቶ ፉኮ ቡቻላ በመጠነኛ የአርሶ አደር ኑሮ የሚተዳደሩ ቢሆኑም ለወንጌል ካላቸዉ መነሳሳትና ለችግረኞች ካላቸዉ ዉስጣዊ ስሜትና ርህራሄ የተነሳ አነሰኝ ጎደለኝ ሳይሉ ችግረኞችን ሲረዱ ፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ስብሰባዎችን ስያደርጉ ፣ እንግዶችን ለመቀበል ሲተጉ ፣ የማምለኪያ ቤቶችን ሲሰሩ እስካሁንም አቅማቸዉ በፈቀደ መልኩ ትጋታቸዉን እየተወጡ መገኘታቸዉን ባደረግንላቸዉ ቃለ መጠይቅ አስቀምጠዋል፡፡ በተጨማሪም ለግላቸዉ ጥቅም ያልኖሩ ራስ ወዳድነት ያልተጠናወታቸዉ አባት ናቸዉ፡፡ ከህይወታቸዉ ምስክርነት እንደተረዳነዉ ለጋሽ ፣ ሩህሩህና የህይወት ምሳሌ መሆን የቻሉ አባት ናቸዉ፡፡ በተለይ ችግረኞችን ከመርዳት አንጻር ሲናገሩ ‹‹ችግረኞችን የሚረዳዉ በቂ ገንዘብ ስላለኝ ወይም ተርፎኝ ምጽዋት ለማዉጣት አይደለም፡፡ ከሌሎች የተሻለ በቂ ንብረት ስላለኝ ሳይሆን ከጉድለቴ ጉድለታቸዉን ለመሸፈን ነዉ›፤ ጉድለታቸዉም ሁል ጊዜ ጉድለቴ ሆኖ ስለምታየኝ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ፣ ምንም ባልችል እንኳን ከሚያለቅሱት ጋር አለቅሳለሁ፣ እጸልይላቸዋለሁ እንጂ ችላ ብዬ አላልፋቸዉም›› ይላሉ፡፡ ንግግራቸዉን በማስተዋል ስናዳምጥ ‹‹ሰዉን ለመርዳት ሰዉ መሆን በቂ ነዉ፡፡›› የሚሉ ይመስላሉ፡፡ ደግሞም ሐዋሪያ ያዕቆብ በያዕ 1፡27 ላይ ‹‹ንጽህ የሆነ ነዉርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሄር አብ ዘንድ ይህ ነዉ፤ ወላጆች የሌላቸዉን ልጆች ፤ ባልቴቶችንም በመከራ መጠየቅ በአለም ከሚገኝ እድፍ እራስን መጠበቅ ነዉ፡፡›› ያለዉን ቃል መሰረት ያደረጉ ይመስላሉ፡፡

ንግግራቸዉን በመቀጠል አቶ ፉኮ  እጅግ በጣም በመገረም ህይወት ሆኖ ስለ ሰላም ይናገራሉ፡፡ ‹‹ለኢትዮጵያ ሰላምን ያመጣ ወንጌል ነዉ ፤ ያንን አስጨናቂ የስደት የግርፋት፣ የእስራት ፣የዘረፋ ፣ የጭንቀት ፣ የባርነት ዘመን ያሳለፈ ፤ በነፃነት ጌታን የሚናመልክበት ዘመን ያሳየን የወንጌል ፍሬ ነዉ›› ይላሉ፡፡ በመቀጠልም ለዚህ ተግባር ምክንያት የሆነዉን የአሁኑን የኢትዮጵያን መንግስት ያመሰግናሉ፡፡ ባለፉት የመንግስት አገዛዝ ዉስጥ በተለይም በደርግ ጊዜ የደረሰባቸዉን ጥልቅ መከራ የሚያስጨንቅ ስሜት በተሞላ አገላለጽ ያስቀምጣሉ፡፡ ‹‹ በደርግ ጊዜ ጌታን በማምለካችን ብቻ ተገርፈናል ፣ ተደብድበናል ፣ ታስረናል ፣ ቤታችን ተቃጥሏል ፤ ቤተክርስቲያን ተቃጥሎብናል ፣ ልጆቻችን ወደ ጦር ሜዳ ተወስዶብናል ፣ ከእኛ ነጥለዉ ብዙ ጓደኞቻችንን ገድለዉብናል ፣ ጌታን በማምለካቸዉ ብቻ ጓደኞቻችን በጥይት ተረሽነዋል፡፡ ብዙ ጓደኞቼ በተገደሉበት ስፍራ በባሌ ዶዶላ እንዲሁም በጎባ ታስሬ ነበር፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ያስመለጠኝና ይህንን ቀን ያሳየኝን ጌታ አመሰግናለሁ›› ይላሉ፡፡

የታቦር ወንጌላዊት ኮሌጅ ራዕይና ተልይኮን ከመደገፋቸዉ አንጻር ሲናገሩ ሁል ጊዜ በጸሎት ከታቦር ወንጌላዊ ኮሌጅ ጎን እንዳሉና በየእለቱ ለዚህ ተልዕኮ ስኬት እንደሚቃትቱም ተናግረዋል፡፡  አቶ ፉኮ ቡቻላ ማንም ሳያነሳሳቸዉ ፣ ማንም ሳይጠይቃቸዉ ላለፉት ሁለት አመታት በጸሎትና አቅማቸዉ በፈቀደላቸዉ የታቦር ወንጌላት ኮሌጅን ራዕይ ሲደግፉ መቆየታቸዉ ግልጽ ነዉ፡፡ በዚህ ዘመን የሚሽን ትምህርት ቤት መኖርና የእግዚአብሄርን ቃል ማስተማር ብቻ ያስደሰታቸዉ ይህ አባት ‹‹ተማሪዎች ሻይ ቡና ይጠጡበት በማለት ሁለት ሺ ብር እንደላኩም ይታወቃል፡፡›› የታቦር ወንጌላዊት ኮሌጅ ተማሪዎችም በመስማማት በእሳቸዉ ስም መጽሀፍ ተገዝተዉ በቤተ መጽሐፍት ተቀምጠዉ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ ይህ አባት ይህንን እንዲያደርጉ ያነሳሳቸዉ ምን እንደ ሆነ ጠይቀናቸዉ ነበር፤ የመለሱልን መልስ ግን ያልጠበቅነዉ ነበር፤ ‹‹ስጦታን ሁሉ የሰጠን እግዚአብሄር ነዉ፡፡ የሰጠን ግን ለራሳችን ብቻ እንድንኖርበት አይደለም፤ የሰጠንን እንድንሰጥና እንድንደጋገፍበትም ጭምር ነዉ፡ የዘወትር ጸሎቴ ያለኝ ጥቂት ገንዘብ ለወንጌል ስራ እንዲዉል እንጂ በህክምናና በወንጀል ምክንያት ሐኪሞችና ዳኞች እንዳይበሉ የዘወትር ጸሎቴ ነዉ›› ይላሉ፡፡ ይህ አባት ለሁላችንም ታላቅ ምሳሌ ሊሆኑን ይችላሉ፡፡ ሁላችን ለጋራ ራዕይ በአንድነት ብንያያዝና ብንደጋገፍ ለሌሎች እንተርፋለን አንጂ ሁል ጊዜ ከሌሎች የምንጠብቅ አንሆንም፡፡

በመጨረሻም አቶ ፉኮ ለታቦር ወንጌላዊት ኮሌጅ ተመራቂዎች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸዉ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡ በዚህ ምረቃ ምክንያት በታቦር ወንጌላዊት ኮሌጅ ግቢ  ተገኝተዉ እግዚአብሄር እየስራ ያለዉን ስራ በመመልከታቸዉ የተሰማቸዉን ታላቅ ደስታን ገልጸዋል፡፡ እንዲሁም ወንጌልን በንፁህ ልብና በትጋት ለመስራት እንዲነሱ፤ የማይጠፋዉን የወንጌልን እሳትና የወንጌልን ዘር ይዘዉ እንዲወጡ ለተመራቂዎች፣ ለተመራቂ ቤተሰቦች፣ ለታቦር ወንጌላዊት ኮሌጅ ሰራተኞችና ተማሪዎች በሙሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

‹‹ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጕልበታም ነኝ ጕልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።›› ኢያ 14፡11

ለበለጠ መረጃ ፡ http://taborevan.org/

Advertisements
This entry was posted in Tabor Evangelical College. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s